- ስትራቴጂያዊ የሆኑና የገበያ ክፍተት ያለባቸው የኬሚካል ኢንዱስትሪ ምርቶችን አምርቶ ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ በማቅረብ ለዘላቂ ሀገራዊ ልማት አስተዋፅኦ ማድረግ።
ኮርፖሬሽኑ በተቋቋመበት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የተለያዩ ተግባርና ኃላፊነቶች የተሰጡት ሲሆን እነዚህምየማዳበሪያ፣ የጎማ ዛፍ ውጤቶች፣ የሲሚንቶ፣ ሰልፈሪክ አሲድ፣ ሄድሮጅን ፕርኦክሳይድ፣ ኮስቲክ ሶዳ ፣ ፀረ-ተባይ፣ ፀረ-አረም እና ሌሎች የኬሚካል ምርቶችንና ውጤቶችን በማምረት ለገበያ ማቅረብ፤ የፕሮጀክቶችን ጥናት፣ የዲዛይን ዝግጅት፣ የተከላ እና የምርምር ሥራዎችን መሥራት፤ መመሪያን ተከትሎ ቦንድ መሸጥ፣ በዋስትና ማስያዝ እና ከአገር ውስጥና ከውጭ የገንዘብ ምንጮች ጋር የብድር ውል መደራደርና መፈራረም፤ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በመተባበር የኬሚካል ፋብሪካዎች የማምረቻ መሣሪያዎችና መለዋወጫ ሥራዎች እንዲከናወኑ ማድረግ፤ ለዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ከሚመለከታቸው የትምህርት ተቋማት ጋር መተባበር።
ስልጣንና ተግባር:-