• ቦሌ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

  • ይደውሉ +251-11-662-90-15/662-31-30

  • ይላኩልን chemindcorpo@cic.gov.et

01 መስከረም

ዋና ሥ/አስፈጻሚው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

እንኳን ለአዲሱ ለ2017 ዓመት በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን

ኮርፖሬሸናችን በ2016 ዓ.ም ከወትሮው እጅግ በተሻለ ሁኔታ በመፈፅም ለቀጣይ 2017 በጀት ዓመትም እርሾ የሚሆኑ በርካታ ተመክሮዎችን በማገኘት በተሳካ ሁኔታ አሳልፎታል። ሠራተኛውና አመራሩ በቀጣይ በጀት ዓመትም የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ሁለንተናዊ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ሥራ ገብቷል። ለኮርፖሬሽናችን ሥ/አመራር ቦርድ፣ የሥራ መሪዎች፣ ሠራተኞች እና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ ዓመቱ የጤና፣ የሰላም፣ የብልፅግና እና ተቋማችንን ይበልጥ ከፍ ለማድረግ የምንተጋበትና ምርታማነትን የምናሳድግበት ዘመን እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ። በድጋሚ እንኳን በሠላም አደረሳችሁ፣ መልካም አዲስ ዓመት፡፡ ዶ/ር ኢ/ር ሁንዴሳ ደሳለኝ የኬሚካል ኢ/ኮርፖሬሽን ዋና ሥ/አስፈጻሚ