በኮርፖሬሽኑ የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የጥራት አስተዳደር (ISO 9001:2015) ሰርተፍኬት ባለቤት ሆነ፡፡
በኮርፖሬሽናችን ሥር የመተዳደረው ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የጥራት አስተዳደር (ISO 9001:2015) ሰርተፍኬት ስላገኘ እንኳን ደስ አላችሁ። የተገኘው ውጤት አስተማማኝ ጥራት ያለው ሲሚንቶ ለገበያ የማቅረብ አቅማችንን በማጠናከር በሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ዕድገት የሚኖረንን ሚና የሚያጎለብት ከመሆኑም በላይ ተከታታይ የምርት ደረጃዎች እና ቀጣይነት ያለው መሻሻል በሁሉም ኮርፖሬሽኑ በተሠማራባቸው የሥራ ዘርፎች ላይ ለማስመዝገብ ያለንን የማይናወጥ ቁርጠኝነት ያንፀባርቃል።
