እንኳን ለ2018 አዲስ አመት አደረሰን! የምሥራች፣ እንኳን ደስ አለን!
የቁጭት ዘመናትን አልፈን ወደ ተድላ እና ብልጽግና ለመገስገስ በአፍሪካ ታላቁን የህዳሴ ግድብ ግንባታን በራሳችን አቅም አጠናቀን በማስመረቅ የታሪክ እጥፋት ወቅት ላይ የምንገኝ በመሆናችን የ2018 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓላችንን ዕጥፍ ድርብ ያደርገዋል፤ እንኳን ለዚህ ልዩ ዓመት በሠላም አደረሰን፡፡ በአዲሱ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ ዘመንም መሠል ሜጋ ፕሮጀክቶችን ዕውን ለማድረግ እንደ ሀገር የሚደረገውን ዘርፈ- ብዙ የብልጽግና መዳረሻ ትግል ለማገዝ ኮርፖሬሽናችን የተሠማራበት የሀገሪቱ የኬሚካል ዘርፍ እንዲጎመራና የልማቱ መሠረት እንዲሆን ተደምረን የድርሻችንን ለመወጣት ዝግጅታችንን ጨርሠናል፡፡ በድጋሚ እንኳን ለዚህ የንጋት ማብሠሪያ እና የታሪክ እጥፋት ወቅት በሠላም አደረሳችሁ፣ አደረሠን! በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ፡፡ ሁንዴሳ ደሳለኝ (ዶ/ር እንጂነር )