ኮርፖሬሽኑ የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና የኮርፖሬሽኑ የበላይ ሥራ አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም የኮርፖሬሽኑ ሥ/አመራር ቦርድ ተወካይ በተገኙበት በባቱ ከተማ ነሐሴ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ገመገመ፡፡
ኮርፖሬሽኑ የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አመራር አና ሠራተኞች ጋር ገመገመ። ኮርፖሬሽኑ የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና የኮርፖሬሽኑ የበላይ ሥራ አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም የኮርፖሬሽኑ ሥ/አመራር ቦርድ ተወካይ በተገኙበት በባቱ ከተማ ነሐሴ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ገመገመ፡፡ ከግምገማው በፊት በከተማው የሚገኙት የኮርፖሬሽኑ ተ/ተቋማት የአዳሚቱ/ጸ/ተ/ማ/ፋብሪካ እና የባቱ ኮስቲክ ሶዳ ፋብሪካ የስራ እንቅስቃሴ የመስክ ምልከታ ከተደረገ በኋላ ሲሆን በዕለቱ በኮርፖሬሽኑ የበላይ አመራር የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም ገለጻ ከቀረበ እና በኢንስትመንት ሆልዲንግ የግብረ-መልስ ገለጻ ከቀረበ በኋላ ውይይት ተደርጎበት አፈጻጸሙ እጅግ አመርቂ በተለይም የትርፍ ዕቅድ አፈጻጸሙ በጣም ከፍተኛ(1.611 ቢሊዮን ወይም የዕቅዱን 284.67%) በመሆኑ ሁሉም የኮርፖሬሽኑ ሠራተኛና አመራር አንኳን ደስ ያላችሁ የሚል መልእክት ከመድረኩ ተላልፏል፡፡ በመጨረሻም የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስመልክቶ በኢንስትመንት ሆልዲንግ የበላይ ሀላፊ ከተሰጡ በኋላ የምስጋና ሽልማት ለሚመለከታቸው አመራር አባላት ተበርክቶ ስብሰባው ተጠናቋል፡፡