የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ
በዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን የችግኝ ተከላ ፕሮግራም መርሃ-ግብር ኮርፖሬሽኑ በሥሩ ያሉትን ተጠሪ ተቋማት የሥራ መሪዎችን እና ሠራተኞችን በማሳተፍ በመጀመሪያው ዙር በተጠሪ ተቋማት የማምረቻ ክልል ውስጥ በቁጥር 20105፤ በሁለተኛው ዙር በታጠቅ ሲሚንቶ ፋብሪካ የመዋዕለ ህፃናት ፕሮጀክት ግቢ ውስጥ በቁጥር 230፤ በሦስተኛው ዙር ማለትም በዛሬው ዕለት በሞጆ-ሃዋሳ ፈጣን መንገድ ዳርቻ አንድ ኪ.ሜ. ርቀት በሚያካልል ቦታ፣ በሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ክልል፣ በታጠቅ ሲሚንቶ ፋብሪካ ክልል እና በጎማ ዛፍ ልማትና ምርት ፕሮጀክት አካባቢ በቁጥር 18,887 በአጠቃላይ በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 39,222 ችግኞችን የመትከል ፕሮግራም አካሂዷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሙገር ሲ/ፋ በችግኝ ጣቢያው ያፈላውን 96,500 ልዩ ልዩ ችግኞችን ለአካባቢው ማህበረሰብ በማከፋፈል ለአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የበኩሉን አስተዋፅዎ አበርክቷል፡፡